ቁርአን

የቁርአን ንባብ ሥርዓት

1.    ቁርአንን ከማንበብ በፊት ውዱዕ ማድረግ
2.    ቁርአንን በማንበብ ምንዳ እንደሚገኝ እያሰቡ ማንበብ
ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ከአላህ መጽሐፍ አንድን ፊደል ያነበበ አስር ምንዳን ያገኛል፤አሊፍ ላም ሚም አንድ ፊደል አይደለም ነገር ግን እያንዳንዳቸው በተናጠል ፊደሎች ናቸው” ብለዋል፡፡
3.    በእርጋታ ማንበብ
አላህ እንዲህ ብል “ቁርኣንንም በዝግታ ማንበብን አንብብ (አል ሙዘሚል፡4)
4.    አሳምሮ መቅራት
ነብዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “ቁርአንን በዜማ ያላነበበ ከእኛ አይደለም ብለዋል፡፡(ቡኻሪ ዘግበውታል)በሌላም ሐዲስ ቁርአንን በድምጻችሁ አሳምሩ፤ጥሩ ድምጽ የቁርአንን ውበት ይጨምራልብለዋል(አቡ ዳውድ ዘግበውታል)
5.    እያስተነተኑ መቅራት 
አላህ እንዲህ ብል “ቁርኣንንም አያስተነትኑምን? በእውነቱ በልቦቻቸው ላይ ቁልፎቿ አልሉባትን?”(ሙሀመድ፡24)



ለጠቅላላ እውቀት
ከ114 የቁርአን ሱራዎች መካከል 28ቱ መዲናዊ (በመዲና የወረዱ) ናቸው፡፡
‹በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩኅ በጣም አዛኝ በሆነው› ሁለት ጊዜ የተጠቀሰበት ምዕራፍ ሱራ አን ነምል ነው፡፡(የሱራው መጀመሪያ ላይና አንቀጽ 30 ላይ)
በቁርአን ውስጥ ረጅሙ ቃል ‹ፈአስቀይናኩሙሁ› የሚለው ሲሆን በአረብኛ ሲፃፍ 11 ፊደሎችን ይይዛል፡፡ሱራ አል ሂጀር አንቀጽ 15 ውስጥ ይገኛል፡፡
(ነፋሶችንም (ደመናን) ተሸካሚዎች አድርገን ላክን፡፡ ከሰማይም (ከደመና) ዝናብን አወረድን፡፡ እርሱንም አጠጣናችሁ፡፡ እናንተም ለእርሱ አድላቢዎች አይደላችሁም፡፡)
ቁርአን ውስጥ 14 ቦታዎች ላይ የሱጁድ ምልክት አለ፡፡ሱረቱል ሀጅ 2 የሱጁደ ቦታዎች አሉት፡፡
በቁርአን ውስጥ ሱራዎች የተቀመጡት በአወራረዳቸው ቅደም-ተከተል ሳይሆን በረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የመጨረሻ ረመዳን ወቅት ጂበሪል ነብዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ባስቀራበት ቅደም ተከትል ነው፡፡
በሱራ ደረጃ መጨረሻ እንደወረደ የሚታመነው ሱራ አን ነስር ሲሆን በአንቀጽ ደረጃ ደግሞ ሱራ አል ማኢዳህ አንቀጽ 3 ‹…ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ…› የሚለው ነው፡፡
ቁርአን በሙሉ ጥራዝ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው በአቡበከር(ረ.ዐ) የኸሊፋነት ዘመን ነው፡፡ሰዎች ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ይቀሩበት ከነበረው ዘዬ በተለየ ሁኔታ መቅራት በመጀመራቸው ይህን ልዩነት ለማጥፋት በዑስማን የኸሊፋነት ዘመን አቀራርን የሚያስተካክሉ ‹ሥርዓተ ነጥቦች› ተደርገውለት አሁን ያለበትን ቅርጽ ይዞ ተዘጋጅቷል፡፡
የአንቀጾቹ አይነት የተለያየ ነው፡፡በትረካ መልክ ወረዱ ሱራዎችና አንቀጾች አሉ(የነብያትን ታሪክ የሚገልጹ አንቀጾች፣ሱራ ዩሱፍ)፤ለጥያቄዎች መልስ የሚሰጡ አንቀጾች አሉ (‹ስለሩህም ይጠይቁሀል፡-«ሩሕ ከጌታዬ ነገር ነው ከዕውቀትም ጥቂትን እንጂ አልተሰጣችሁም»በላቸው፡፡)፤ሙሽሪኮችና ሙናፊቆች የተናገሩትን የሚጠቅሱም አሉ(«አማልክቶቹን አንድ አምላክ አደረጋቸውን? ይህ አስደናቂ ነገር ነው»)፤የአላህን ዛትና ሲፋት የሚገልጹ አንቀጾች አሉ(እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አልሉት፡፡)፤የተፈጠሩ ሁኔታዎችን በተመለከተም የወረዱ አሉ (ስለ በድር ጦርነት፣ስለ አዒሻ መታማት…)፤ሀላልና ሀራምን፣ጀነትና ጀሀነምን የሚያብራሩም አንቀጾች አሉ፡፡
ተውሒድን በተመለከተ የወረዱት ብዙዎቹ አንቀጾች መካዊና በነብይነት መጀመሪያ አካባቢ የወረዱ ናቸው፡፡በ‹እናንተ ሰዎች ሆይ› ፣ ‹በእናንተ አማኞች ሆይ› የሚጀምሩት አንቀጾችም እንዲሁ በብዛት የኢስላም ጥሪ በተጀመረበት ጊዜ በመካ የወረዱ ናቸው፡፡በ‹የስአሉነከ› (ሙሀመድ ሆይ ይጠይቁሀል) በሚል የሚጀምሩት፣ አስጠንቃቂ የሆኑት፣የኢስላምን ህግና ደንብ የያዙትና የሚያብራሩት አንቀጾች መዲናዊ ናቸው፡፡ይህም ማለት ሙስሊሞች ተደላድለው ያለ ፍርሀት መኖር ሲጀምሩ የወረዱ ናቸው ማለት ነው፡፡
  




የአያተል ኩርሲ ጥቅሞች
--ከቤት ሲወጣ አያተል ኩርሲን መቅራት 70.000 መላኢኮች እንዲጠብቁን ያደርጋል
--ወደቤት ሲገባ አያተል ኩርሲን መቅራት ድህነት ወደቤት እንዳይገባ ያደርጋል
--ከውዱዕ በኋላ አያተል ኩርሲን መቅራት አላህ ዘንድ ደረጃችንን በ70 እጥፍ ይጨምራል
--ከመኝታ በፊት አያተል ኩርሲን መቅራት ለሌሊቱ 1 የመላኢካ ጥበቃ እንዲመደብልን ያደርጋል
--ከፈርድ ሰላት አያተል ኩርሲን መቅራት በኛና በጀነት መካከል የሚኖረው ሞት ብቻ ነው፡፡
(በአላህ ፈቃድ ይህ ሁሉ ይሆናል)

No comments:

Post a Comment